Fana: At a Speed of Life!

አትክልት ተራ ወደ ጃንሜዳ እንዲዛወር ተወሰነ

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 23 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) አትክልት ተራ ወደ ጃንሜዳ እንዲዛወር ተወሰነ።
 
የአዲስ አበባ ምክትል ከንቲባ ኢ/ር ታከለ ኡማ ከከተማው የፀጥታ አካላት ጋር አትክልት ተራ አካባቢ እየታየ ባለው መጨናነቅ ዙሪያ ተወያይተዋል።
 
ቦታው የከተማዋ ከፍተኛ የአትክልት ምርት ማከፋፈያ ሲሆን ከፍተኛ የሰው ጭንቅንቅ በየእለቱ የሚታይበትና ከኮሮና ቫይረስ ጋር በተያያዘም ለቁጥጥር አስቸጋሪ መሆኑ ተገምግሟል።
 
ስለሆነም ከመጪው ሰኞ ጀምሮ የአትክልት ግብይቱ በጊዜያዊነት ወደ ጃንሜዳ እንዲዘዋወር ተወስኗል።
 
አትክልት ተራ ለጊዜው ለነጋዴዎቹ እንደ እቃ ማስቀመጫ(ስቶር) ብቻ እንዲያገለግል ተወስኗል።
 
ጃንሜዳ ቦታው ሜዳማ እንደመሆኑ ለእንቅስቃሴ ምቹ መሆኑና ለቁጥጥር አመቺ መሆኑ ግምት ውስጥ በማስገባት ነው የአትክልት ግብይቱ ወደ ጃንሜዳ እንዲዘዋወር መደረጉን የከንቲባ ፅህፈት ቤት አስታውቋል።
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.