Fana: At a Speed of Life!

ሊዮኔል ሜሲ የፒ ኤስ ጂ ቆይታውን ለማራዘም ተስማማ

አዲስ አበባ፣ ታኅሣሥ 15፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) አርጀንቲናዊው ኮከብ ሊዮኔል አንድሬስ ሜሲ የፈረንሳዩ ፒ ኤስ ጂ ቆይታውን ለአንድ ዓመት ለማራዘም ከክለቡ ጋር ስምምነት ላይ መድረሱ ተሰማ፡፡

በሣምንቱ መጀመሪያ የስፔኑ ክለብ ባርሴሎና ፕሬዚዳንት ጆአን ላፖርታ÷ “ሜሲ 21 ዓመታትን ወዳሳለፈበት የቀድሞ ክለቡ ባርሴሎና ቢመለስ ደስ ይለኛል” ማለታቸውን ተከትሎ የሜሲ ጉዳይ ከባርሴሎና ጋር ቢያያዝም እንደማይሔድ መረጋገጡን ቢቢሲ ስፖርት ያወጣው መረጃ አመላክቷል፡፡

በፒ ኤስ ጂ የእግር ኳስ ዳይሬክተር ሉዊስ ካምፖስ እና ሊዮኔል ሜሲ አባት መካከል በኳታር የተደረገውን ውይይት ተከትሎ ሜሲ ከፒ ኤስ ጂ ጋር የአንድ ዓመት ውል ለማራዘም ስምምነት ላይ ደርሷል ነው የተባለው፡፡

ሊዮኔል ሜሲ ለፒ ኤስ ጂ 53 ጊዜ ተሰልፎ በፈረንሳይ ሊግ አንድ ሁሉም ውድድሮች 23 ጎሎችን ማስቆጠር ችሏል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.