Fana: At a Speed of Life!

በ200 ሚሊየን ዶላር እየተገናባ የሚገኘው የአልባሳት ክር ማምረቻ ፋብሪካ የመጀመሪያው ዙር ግንባታ ተጠናቀቀ

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 23 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) በ200 ሚሊየን ዶላር በአዳማ ኢንዱስትሪያል ፓርክ እየተገናባ የሚገኘው የአልባሳት ክር ማምረቻ ፋብሪካ የመጀመሪያው ዙር ግንባታ ተጠናቀቀ።

ኪንግደም የክር ማምረቻ ኩባንያ በአዳማ ኢንዱስትሪያል ፓርክ በሁለት ዙር በአፍሪካ ትልቁን የክር ፋብሪካ እየገነባ እንደሚገኝ የኢንቨስትመንት ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ አበበ አበባየሁ በትዊተር ገፃቸው ላይ አስፍረዋል።

ፋብሪካው ወደ ስራ ሲገባም በዓመት ከፍተኛ ጥራት ያለው 5 ሺህ ቶን የአልባሳት ክር በዓመት እንደሚያመርት ነው ኮሚሽነሩ የገለፁት።

በ32 ሄክታር መሬት ላይ ያረፈው ፋብሪካው ሙሉ በሙለ ወደ ምርት ሲገባ ለ4 ሺህ ዜጎች የስራ እድል እንደሚፈጥር ይጠበቃል።

በዓለም ላይ ከፍተኛው የአልባሳት ክር አምራች የሆነው ኩባንያው የአለምን የአልባሳት ክር 10 በመቶ እንደሚሸፍን መረጃዎች ያመለክታሉ።

ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ!
https://t.me/fanatelevision

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.