Fana: At a Speed of Life!

የሁለተኛው ዙር የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ተፈታኞች ወደ መፈተኛ ዩኒቨርሲቲዎች መግባት ጀመሩ

አዲስ አበባ፣ ታኀሣሥ 15፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የሁለተኛው ዙር የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና የሚወስዱ ተፈታኞች ወደ መፈተኛ ዩኒቨርሲቲዎች መግባት ጀምረዋል፡፡

እስካሁን ቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ የሁለተኛ ዙር የ12ኛ ክፍል መልቀቀቂያ ተፈታኞችን መቀበል ጀምሯል፡፡

በዚህም ከሁለቱ ጉጂ ዞኖች እና ከነገሌ ከተማ አስተዳደር በተለያየ ምክንያት በመጀመሪያው ዙር ያልተፈተኑ ከ4 ሺህ 700 በላይ ተማሪዎችን ለመፈተን አስፈላጊውን ዝግጅት አጠናቆ ዛሬ መቀበል መጀመሩን የዩኒቨርሲቲው መረጃ ያመላክታል፡፡

የሁለተኛውን ዙር የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ብሔራዊ ፈተና የሚወስዱ ተፈታኞች ከታኅሣሥ 15 እስከ 16 ወደ ተመደቡበት የመፈተኛ ዩኒቨርሲቲ እንደሚገቡ እና ታኅሣሥ 17 በፈተናው ሂደት ላይ ገለጻ (ኦረንቴሽን) እንደሚሰጥ ተገልጿል፡፡

እንዲሁም ከታህሳስ 18 እስከ 21 ቀን 2015 ዓ.ም ድረስ ደግሞ ፈተናው እንደሚሰጥ የወጣው መርሐ ግብር ያመላክታል፡፡

በመስከረም መጨረሻ እና ጥቅምት መጀመሪያ የተሰጡት የ12ኛ ክፍል የፈተና አሰጣጥ ሂደት ስኬታማ እንደነበር እና ፈተናውን ለመውሰድ ከተመዘገቡት ውስጥም 98 ነጥብ 9 በመቶዎቹ በዩኒቨርሲቲዎች ቀርበው ፈተናቸውን እንዲወስዱ መደረጉን ትምህርት ሚኒስቴር ማሳወቁ ይታወሳል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.