Fana: At a Speed of Life!

ያለውን ፀጋ በመጠቀም የሌማት ትሩፋትን እውን ለማድረግ መረባረብ አለብን – አቶ ደመቀ መኮንን

አዲስ አበባ፣ ታኅሣሥ 16፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ያለውን ፀጋ በመጠቀም የሌማት ትሩፋትን እውን ለማድረግ መረባረብ አለብን ሲሉ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ጥሪ አቀረቡ፡፡

በደቡብ ክልል የወተት፣ የዶሮ፣ የስጋና የማር ምርት ማሻሻያ ማስተዋወቂያ መርሐ ግብር በጉራጌ ዞን መስቃን ወረዳ እየተካሄደ ነው፡፡

በሌማት ትሩፋት ክልሉን በቅርበት እንዲደግፉ የተመረጡት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን በመድረኩ ላይ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

በመልዕክታቸውም ፥ በአርባ ምንጭ ከተማ የተጀመረው ሀገራዊ መርሐ ግብር በተለያዩ አካባቢዎች በማስተዋወቅ ተግባራዊ እንዲሆን እየሰራን እንገኛለን ብለዋል፡፡

አክለውም ‘’የሌማት ትሩፋት’’ ትርጉም ቤቱ ሙሉ ይሁን ማለት እንደሆነ አንስተው ፥ ይህም ለኢትዮጵያ ህዝብ አዲስ አይደለም በባህላዊ ምርቃቱ ያውቀዋልም ነው ያሉት ።

በተመጣጠነ ምግብ ጤናው የተጠበቀ ትውልድን ማፍራት ይገባል ያሉት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ፥ በአካባቢው ያለውን ፀጋ በመጠቀም የሌማት ትሩፋትን እውን ለማድረግ መረባረብ አለብንም ነው ያሉት፡፡

በምንተስኖት ሙሉጌታ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.