Fana: At a Speed of Life!

ሀገራዊ የአደጋ ስጋት ቅድመ ማስጠንቀቂያ ሰነድ ይፋ ሆነ

አዲስ አበባ፣ ታኅሣሥ 17፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ሀገራዊ የአደጋ ስጋት ቅድመ ማስጠንቀቂያ ጥናት ሰነድ ይፋ መደረጉን የብሔራዊ አደጋ ስጋት አመራር ኮሚሽን አስታወቀ፡፡
 
ጥናቱ በኢትዮጵያ በተለያዩ አካባቢዎች ሊከሰቱ የሚችሉ የተፈጥሮና ሰው ሰራሽ አደጋዎች የሚያደርሱትን ቀውስ እና ጉዳት መቀነስ የሚያስችል መሆኑ ተገልጿል፡፡
 
በመንግስት እና አጋር ድጅቶች ድጋፍ በተደረገው በዚህ ጥናት÷በሁሉም ክልሎች በተለዩ 491ወረዳዎች የቅድመ ማስጠንቂያ ሰነድ መዘጋጀቱ ተጠቁሟል፡፡
 
ሰነዱ በአካባቢዎቹ ሊከሰት የሚችለው ችግር ምንድን ነው፣ ችግሩን ለመከላከል እና ለመቋቋም ያለው አቅም ምን ይመስላል የሚሉ እና መሰል ተያያዥ መረጃዎችን ያካተተ ነው ተብሏል፡፡
 
በሌላ በኩል በመላ ሀገሪቱ ለሚገኙ 434 ወረዳዎች የተላምዶ መኖር እና የመጠባበቂያ እቅድ ሰነድ የተዘጋጀላቸው መሆኑ ተመላክቷል፡፡
 
ክልሎች የልማት ስራ እቅዳቸውን አደጋን በመከላከል ላይ መሰረት አድርገው እንዲያከናውኑ ሰነዶቹ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንዳላቸው የኮሚሽኑ ኮሙኑኬሽን ዳይሬክት አቶ ደበበ ዘውዴ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ተናግረዋል፡፡
 
የቅድም ማስጠንቀቂያ ተግባራትን በተዘጋጀው የጥናት ሰነድ አማካኝነት መከወን ከተቻለም የድርቅ፣ ጎርፍ እና መሰል አደጋዎችን የመከላከል አቅምን ማሳደግ እንደሚቻል አስረድተዋል፡፡
 
 
በመላኩ ገድፍ
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.