Fana: At a Speed of Life!

ሰላም የትግራይ ህዝብ ፅኑ ፍላጎት መሆኑን የክልሉ ነዋሪዎች ተናገሩ

አዲስ አበባ ፣ ታኅሣሥ 17 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ሰላም የትግራይ ህዝብ ፅኑ ፍላጎት መሆኑን ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ያነጋገራቸው የክልሉ ነዋሪዎች ተናገሩ።

ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት በተለያዩ የትግራይ ክልል ከተሞች ተዘዋውሮ ያነጋገራቸው የህብረተሰብ ክፍሎች ህዝቡ በጦርነት እንደተጎዳ ተናግረዋል።

የትግራይ ህዝብ በተለያየ ጊዜ ከተደረጉ ጦርነቶች ያተረፈው ኪሳራ ብቻ መሆኑን በመረዳት ይህ ሁኔታ ሊደገም አይገባም ነው ያሉት።

የሽራሮ፣ ሽረ እና የሌሎች ከተሞች ነዋሪዎች ጦርነት ለበርካቶች ሞትና ስደት፣ ለመሰረተ ልማት ውድመትና መፈራረስ ምክንያት መሆኑን በመግለፅ ሰላም የህዝቡ ምርጫ እንደሆነ ገልጸዋል።

የፕሪቶሪያውን የሰላም ስምምነት ተከትሎ ከጦርነት ፋታ ማግኘታቸውን፣ የሰብዓዊ ረድኤት እየቀረበ መሆኑንና መሰረታዊ አገልግሎት መመለስ መጀመራቸውን በማንሳትም ይህ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጠይቀዋል።

ሁሉም ወገን ለሰላም ቅድሚያ በመስጠት የሰላም ሁኔታውን እንዲያፀናም ነው የጠየቁት ።

በአፈወርቅ እያዩና ለይኩን ዓለም

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.