Fana: At a Speed of Life!

በፕሪሚየር ሊጉ ባህርዳር ከነማ እና ወላይታ ድቻ ድል ቀንቷቸዋል

አዲስ አበባ፣ ታኅሣሥ 17፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በቤትኪንግ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ዛሬ በተደረጉ የ7ኛ ሳምንት ተስተካካይ ጨዋታዎች ባህርዳር ከነማ እና ወላይታ ድቻ ድል ቀንቷቸዋል፡፡

ምሽት አንድ ሰዓት ላይ አርባ ምንጫ ከነማን የገጠመው ባህርዳር ከነማ ኦሴ ማውሊ ባስቆጠራቸው ግቦች 2 ለ 0 በሆነ ውጤት አሸንፏል፡፡

ውጤቱን ተከትሎም የጣና ሞገዶቹ ከመሪው ኢትዮጵያ መድን ጋር ያላቸውን የነጥብ ልዩነት ወደ አንድ ማጥበብ ችለዋል፡፡

በሌላ በኩል ቀደም ሲል በተከናወነ ጨዋታ ወላይታ ድቻ ለገጣፎ ለገዳዲን 4 ለ 3 በሆነ ውጤት በማሸነፍ ወሳኝ ሶስት ነጥብ አግኝቷል፡፡

ውጤቱን ተከትሎም ወላይታ ድቻ አራት ደረጃዎችን በማሻሻል ከሃዋሳ ከተማ ጋር በእኩል 19 ነጥብ 5ኛ ደረጃ ላይ መቀመጥ ችሏል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.