Fana: At a Speed of Life!

በሽረ ከተማ እና አካባቢው መንግስት እያቀረበ ያለው ሰብዓዊ እርዳታ ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል-ነዋሪዎች

አዲስ አበባ፣ ታኅሣሥ 18፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በትግራይ ክልል በሽረ ከተማ እና አካባቢው መንግስት እያደረገ ያለው የሰብዓዊ አቅርቦት ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባ ነዋሪዎች ተናገሩ፡፡

በከተማዋ እና በዙሪያዋ ለሚገኙ ማህበረሰቦች እየተደረገ ያለው የሰብዓዊ አቅርቦት በጦርነቱ ወቅት የተፈጠረውን ችግር የሚያቃልል መሆኑን ነዋሪዎች ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ተናግረዋል።

መንግስት በፕሪቶሪያ እና በናይሮቢ በተደረሰው ስምምነት መሰረት የሚጠበቅበትን እየተወጣ ነው ያሉት ነዋሪዎቹ የተጀመረው ተግባርም ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጠይቀዋል።

እስካሁን ባለውም 151 የሰብዓዊ አቅርቦት የጫኑ ተሽከርካሪዎች ወደ አካባቢው ገብተው እርዳታውን እያከፋፈሉ መሆናቸው ተገልጿል።

የሽረ ከተማ እና የአካባቢው ነዋሪዎች የሰብዓዊ አቅርቦቱ የብዙ ዜጎችን ሕይወት የሚታደግ መሆኑንም ነው የተናገሩት፡፡

በአካባቢው ከመንግስት በተጨማሪ ዓለም አቀፍ የተራድኦ ድርጅቶች የሰብዓዊ እርዳታ እያቀረቡ መሆኑም ነው የተነገረው።

በአፈወርቅ እያዩና ለይኩን ዓለም

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.