Fana: At a Speed of Life!

682 ኢትዮጵያውያን ከሳዑዲ ዓረቢያ ወደ ሀገራቸው ተመለሱ

አዲስ አበባ፣ ታኅሣሥ 18፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ዛሬ በሁለት ዙር በተከናወነ በሳዑዲ ዓረቢያ በችግር ያሉ ዜጎችን የመመለስ ስራ 682 ኢትዮጵያውያንን ወደ ሀገራቸው መመለስ መቻሉ ተገለፀ፡፡

ወደ ሀገር ከተመለሱት 682 ዜጎች ውስጥ 673 ወንዶች፣ 7 ሴቶች እና 2 እድሜያቸው ከ18 አመት በታች የሆኑ ታዳጊዎች ናቸው፡፡

ለተመላሽ ዜጎች በአውሮፕላን ማረፊያና በማቆያ ማእከላት ተገቢውን ድጋፍ እና እንክብካቤ በማድረግ ከቤተሰብ ጋር የመቀላቀል ስራ እየተሰራ እንደሚገኝ ከሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ከህዳር 12 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ እስካሁን በተከናወነ ዜጎችን ወደ ሀገር የመመለስ ስራ 18 ሺህ 962 ኢትዮጵያውያንን መመለስ ተችሏል ተብሏል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.