Fana: At a Speed of Life!

የስራ ዘመናቸው አጠናቀው ወደ አገራቸው ለተመለሱ አምባሳደሮች እውቅና ተሰጠ

አዲስ አበባ፣ ታኅሣሥ 18፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያን በመወከል በተለያዩ አገራት በአምባሳደርነት አገልግለው የስራ ዘመን ቆይታቸውን አጠናቀው ወደ አገራቸው ለተመለሱ አምባሳደሮች እውቅና ተሰጠ፡፡
የምስጋና እና የእውቅና መርሃ ግብሩ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን በተገኙበት ተዘጋጅቶላቸዋል።
እውቅና የተሰጣቸው አምባሳደሮችም አምባሳደር ተሾመ ቶጋ፣ አምባሳደር ታየ አፅቀስላሴ፣ አምባሳደር አለማየሁ ተገኑ ፣አምባሳደር አቡዱልፈታ አብዱላሂ፣አምባሳደር ሱሌይማን ደደፎ፣አምባሳደር ዘነበ
ከበደ፣አምባሳደር ረታ አለሙ፣አምባሳደር ትዝታ ሙሉጌታ ናቸው፡፡
እንዲሁም አምባሳደር ሙሉ ሰለሞን፣ አምባሳደር ወይንሸት ታደሰ፣ አምባሳደር ሄኖክ ተፈራ፣ አምባሳደር ሀሰን ታጁ፣ አምባሳደር መለስ ዓለምና አምባሳደር አለምፀሃይ መሰረት ይገኙበታል።
በዚህም አምባሳደሮቹ የተዘጋጀላቸውን የምስጋና የምስክር ወረቀት ከአቶ ደመቀ መኮንን እጅ መቀበላቸውን ከውጭጉዳይ ሚኒስቴር ቃልአቀባይ ፅህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.