Fana: At a Speed of Life!

ዓመታዊው የቅዱስ ገብርኤል በዓለ ንግስ በቁልቢ እና በሐዋሳ በድምቀት እየተከበረ ነው

አዲስ አበባ፣ ታኅሣሥ 19፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በአመት ሁለት ጊዜ በታኅሣሥ እና በሐምሌ 19 በድምቀት የሚከበረው የቅዱስ ገብርኤል ዓመታዊ የንግስ በዓል ዘንድሮም በታላቅ ሃይማኖታዊ ሥነ ሥርዓት እተከበረ ነው፡፡

በቁልቢ በመከበር ላይ በሚገኘው የንግስ በዓል ላይ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ፓትሪያርክ ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ማቲያስ መገኘታቸው ታውቋል፡፡

በዓሉ ከተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች የመጡ የእምነቱ ተከታዮች በድምቀት እየተከበረ ሲሆን፤ የክብረ በዓሉን ድምቀት ለመመልከት ከተለያዩ የዓለም ክፍሎች የመጡ ጎብኚዎችም በስፍራው መገኘታቸውን በአካባቢዎቹ የተገኙ ባልደረቦቻችን መመልከት ችለዋል።

በዓሉ ከዋዜማው ጀምሮ በተለያዩ መርሐ ግብሮች በድምቀት ሲከበር የቆየ ሲሆን ከትናንት ማምሻ ጀምሮም ከሀገሪቱ የተለያዩ አቅጣጫዎች ወደ ሁለቱም አካባቢዎች ባቀኑ የበዓሉ ታዳሚዎች ከተሞቹ ደምቀዋል።

በዓሉ በርካታ ምዕመናን በተገኙበት በድምቀት እየተከበረ እንደሚገኝም ለማወቅ ተችሏል፡፡

በመቅደስ አስፋው፣ ደብሪቱ በዛብህ እና በቲያ ኑሬ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.