Fana: At a Speed of Life!

ሩሲያ የነዳጅ ዋጋ ጣሪያ ለቆረጡ ሀገራት ነዳጅ እንዳይሸጥ አገደች

አዲስ አበባ፣ ታኅሣሥ 19፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ሩሲያ የነዳጅ ዋጋ ጣሪያቸውን ለቆረጡ ምዕራባውያን ሀገራት ነዳጅ እንዳይሸጥ የሚያግድ ውሳኔ አሳለፈች፡፡

ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን የነዳጅ ዋጋ ጣሪያ ለቆረጡ ሀገራት ነዳጅ እንዳይሸጥ የሚያግደው የውሳኔ አዋጅ ላይ ፈርመዋል።

ፕሬዚዳንቱ እንዳስታወቁት ÷ የምዕራቡ ዓለም ሀገራት አንድ ላይ በማበርና ሞስኮን ለመጉዳት በማሰብ በነዳጅ ዋጋ ጣሪያ ላይ ሥምምነት ላይ ደርሰዋል፡፡

በመሆኑም የነዳጅ ዋጋ ጣሪያ ላይ ውሳኔ ያሳለፉት የአውሮፓ ኅብረት ፣ የቡድን 7 አባል ሀገራት ፣ እንዲሁም አውስትራሊያ የእጃቸውን ማግኘት አለባቸው ብለዋል ፑቲን፡፡

የሩሲያ መንግስት በድረ-ገጽ ባወጣው አዋጅ መሠረት ከላይ በተገለጹት ሀገራት ላይ የተጣለው የነዳጅ አቅርቦት ዕግድ ከፈረንጆቹ የካቲት 1 ቀን 2023 ጀምሮ ተግባራዊ እንደሚሆን እና እስከ ሐምሌ 1 ቀን 2023 እንደሚቆይ ተመላክቷል፡፡

የነዳጅ አቅርቦት ዕገዳው ይቀጥል ወይስ ይነሳ በሚለው ላይ መንግስት በቀጣይ ይወስናልም ተብሏል፡፡

ፕሬዚዳንቱ አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ ለሀገራት የነዳጅ እና የዘይት ውጤቶች አቅርቦት ልዩ ፍቃድ ሊሰጡ እንደሚችሉም በአዋጁ ላይ የተመለከተው።

የሩሲያ የኃይል ሚኒስቴርም አጸፋዊ እርምጃዎቹ የፕሬዚዳንቱን ትዕዛዝ ባከበረ መልኩ እየተፈፀሙ መሆናቸው እንደሚቆጣጠር መግለጹን አር ቲ ዘግቧል፡፡

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.