እስካሁን ከ31 በላይ በሆኑ ከተሞች የቴሌኮም አገልግሎት ዳግም ጀምሯል
አዲስ አበባ፣ ታኅሣሥ 19፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የቴሌኮም አገልግሎት ተቋርጦባቸው ከነበሩ አካባቢዎች መካከል እስካሁን ከ31 በላይ በሚሆኑ ከተሞች አገልግሎቱ ዳግም መጀመሩን ኢትዮ ቴሌኮም አስታወቀ፡፡
በዚሁ መሰረት፡-
👉 በዛሬው ዕለት መቀሌ፣ ውቅሮ፣ ኪሓ እና አባላ የቴሌኮም አገልግሎት አግኝተዋል፡፡
👉 ከዚህ ቀደም 27 ከተሞች አገልግሎቱን ማግኘታቸው ይታወሳል፡፡
👉 በግጭቱ ምክንያት የቴሌኮም አገልግሎት ከተቋረጠባቸው አካባቢዎች መካከል እስካሁን ከ31 በላይ ከተሞች ዳግም አገልግሎት አግኝተዋል፡፡
👉 አገልግሎቱን መልሶ ለማስጀመር ዘጠኝ የቴክኒካል ቡድኖች በአራት አቅጣጫዎች ተሰማርተዋል፡፡
👉 በዚህም ከ981 ኪሎ ሜትር በላይ የፋይበር መገናኛ መስመር ጥገና ማከናወን ተችሏል፡፡
👉 90 የሞባይል ሳይቶችን ዳግም በማገናኘት የስልክ ጥሪ በተሳካ ሁኔታ ተከናውኗል፡፡
👉 61 የባንክ ቅርንጫፎች ዳግም ወደ አገልግሎት የሚመለሱበት ሁኔታ ተፈጥሯል፡፡
👉 የቴሌኮም አገልግሎቱን በሙሉ አቅም ለማስቀጠል የጥገና ሥራው ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተገልጿል፡፡
👉 አገልግሎቱ ከረጅም ጊዜ በኋላ እንደመጀሩ የኔትወርክ መጨናነቅ ሊኖር ስለሚችል ደንበኞች ሁኔታውን እንዲገነዘቡ የኩባንያው ዋና ሥራ አሥፈጻሚ ፍሬሕይወት ታምሩ ጠይቀዋል፡፡