Fana: At a Speed of Life!

በሰሜኑ የሀገሪቱ ክፍል ግጭት በነበረባቸው አካባቢዎች ነዳጅ የሚያከፋፍሉ 14 ኩባንያዎች በቀጥታ ከጅቡቲ ነዳጅ እንዲጭኑ ተፈቀደ

አዲስ አበባ፣ ታኅሣሥ 20፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የነዳጅና ኢነርጂ ባለስልጣን ግጭት በነበረባቸው የሰሜን ኢትዮጵያ አካባቢዎች ነዳጅ የሚያከፋፍሉ 14 ኩባንያዎች በቀጥታ ከጅቡቲ ነዳጅ እንዲጭኑ መፍቀዱን አስታወቀ፡፡
በባለስልጣኑ የነዳጅ አቅርቦት፣ ሎጅስቲክስና ክትትል ዳይሬክተር አቶ ፈቃዱ ሹመት ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደገለጹት÷ በቀጥታ ከጅቡቲ ነዳጅ እንዲጭኑ ፈቃዱ የተሰጣቸው 14 ነዳጅ አከፋፋይ ኩባንያዎች በሰሜን ኢትዮጵያ ከተከሰተው ግጭት በፊት ግጭቱ በነበረባቸው አካባቢዎች ይሠሩ የነበሩ ናቸው፡፡
በግጭቱ ምክንያት የነዳጅ አቅርቦት ተቋረጦባቸው በነበሩ አካባቢዎች ያለውን ነዋሪ በፍጥነት ተጠቃሚ ለማድረግ መንግሥት ያሳለፈው ውሳኔ መሆኑም ተገልጿል፡፡
እንደ ሀገር እየተንቀሳቀሱ ካሉት 43 ነዳጅ አከፋፋይ ኩባንያዎች መካከል ሰሜኑ የሀገሪቱ ክፍል ግጭት በነበረባቸው አካባቢዎች አገልግሎቱን ለሚያቀርቡ 14 ነዳጅ አከፋፋይ ኩባንያዎች በቀጥታ ከጅቡቲ ነዳጅ እንዲጭኑ ፈቃድ መሰጠቱትን ነው አቶ ፈቃዱ ያረጋገጡት፡፡
በባለስልጣኑ የሕዝብ ግንኙነት እና ኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር በቀለች ኩማ በበኩላቸው ፈቃዱን ያገኙት ኩባንያዎችም÷ የተባበሩት፣ ኖክ፣ ኦይል ሊቪያ፣ ቶታል፣ ታፍ፣ ናይል፣ ዳሎል፣ ጎመጁ፣ ሐበሻ፣ አለፋይ፣ ዴልታ፣ ባሮ፣ እስካይ እና ኩምቢ መሆናቸውን አብራርተዋል፡፡

 

በዮሐንስ ደርበው

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.