Fana: At a Speed of Life!

በቻን የአፍሪካ ሀገራት ውድድር የተሻለ ውጤት ለማምጣት እንሰራለን – አሰልጣኝ ውበቱ አባተ

አዲስ አበባ፣ ታኅሣሥ 20፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በቻን የአፍሪካ ሀገራት ውድድር የተሻለ ውጤት ለማምጣት እንሰራለን ሲሉ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን አሰልጣኝ ውበቱ አባተ ገለጹ።

አሰልጣኝ ውበቱ በአልጀሪያ የሚካሄደውን 7ኛው የቻን የአፍሪካ ሀገራት ውድድር ላይ ለመሳተፍ ብሄራዊ ቡድኑ ያደረጋቸውን ዝግጅቶች አስመልክተው መግለጫ ሰጥተዋል።

በመግለጫቸውም÷ የኢትዮጵያ  ብሄራዊ ቡድን ተጋጣሚዎቹን ደቡብ ሱዳን እና ሩዋንዳን በማሸነፍ በመድረኩ የሚሳተፍበትን እድል ማግኘቱን አንስተዋል።

ብሄራዊ ቡድኑ ያደረጋቸው የምድብ ጨዋታዎች ስኬታማ እንደነበሩ የጠቀሱት አሰልጣኙ÷ተጫዋቾቹ የብሄራዊ ቡድን ስሜት እንዲኖራቸው የክትትል ስራዎች ሲሰሩ መቆየታቸውን ተናግረዋል።

የውድድሩ ቀን መቃረቡን ተከትሎም ለ28 ተጫዋቾች ጥሪ መደረጉን ጠቅሰው÷26 ተጫዋቾችም በተቀመጠው የጊዜ ገደብ በመገኘት ልምምድ እያደረጉ መሆናቸውን አብራርተዋል።

ዳዋ ሆጤሳ፣ አማኑኤል ዮሃንስ፣ አስራት ቱንጆ እና ያሬድ ባየ በጉዳት ምክንያት ከስብስቡ ውጭ ናቸው ተብሏል፡፡

ጌታነህ ከበደ እና ታፈሰ ሰለሞን ጥሪ ከተደረገበት ቀን በመዘግየታቸው ከብሄራዊ ቡድኑ መቀነሳቸውንም አሰልጣኙ አብራርተዋል።

በሚኪያስ አየለ

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.