Fana: At a Speed of Life!

የገቢዎች ሚኒስቴር የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝን ለመከላከል ከ14 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት የቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 24፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የገቢዎች ሚኒስቴር ከተጠሪ ተቋማት ጋር በጋራ በመሆን የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝን ለመከላከል ከ14 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት የቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ።
 
ድጋፉ የተደረገው በኢትዮጵያ የተከሰተውን የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝን ለመከላከል የሚደረገውን ጥረት ለማገዝ መሆኑም ተገልጿል።
 
ድጋፉ ለፌደራል እና ለአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ድጋፍ አሰባሳቢ ግብረ ሀይል በዛሬው እለት ተበርክቷል።
 
ድጋፋ በአይነት ከ12 ሚሊየን በላይ መሆኑም ተመላክቷል፡፡
 
በዚህም ለአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከ7 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመቱ የምግብና ፍጆታ እቃዎች ድጋፍ አድርጓል።
 
በሌላም በኩል ከገቢዎች ሚኒስቴርና ተጠሪ ተቋማት ሰራተኞች የተዋጣ 2 ሚሊየን ብር እና ከ4 ሚሊየን ብር በላይ ግምት የሚያወጡ ለምግብ ፍጆታ የሚውል ድጋፍ ለፌዴራል ድጋፍ አሰባሳቢ ግብረ ሀይል ተበርክቷል።
 
ድጋፋን ያበረከቱት የገቢዎች ሚኒስትር አቶ ላቀ አያሌው ሲሆኑ፥ የፌደራል ድጋፍ አሰባሳቢ ግብረ ሀይል ኮሚቴ ምክትል ሰብሳቢ አምባሳደር ምስጋናው አረጋ እና አዲስ አበባ ድጋፍ አሰባሳቢ ግብረ ሀይል አባል የሆኑት አቶ ዮናስ አረጋይ ድጋፉን ተረክበዋል።
 
በትዝታ ደሳለኝ
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.