Fana: At a Speed of Life!

የሰላም ስምምነቱን አፈጻጸም የሚቆጣጠር እና የሚያረጋግጥ ቡድን መቋቋሙን እናደንቃለን- አንቶኒ ብሊንከን

አዲስ አበባ፣ ታኅሣሥ 21፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የሰላም ስምምነቱን አፈጻጸም የሚቆጣጠር፣ የሚያረጋግጥና የሚያስከብር የአፍሪካ ህብረት ቡድን መቋቋሙን አሜሪካ እንደምታደንቅ የአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን ገለጹ፡፡

አሜሪካ በፌዴራል መንግስት እና በህዋሃት መካከል የተደረሰው ስምምነት ተግባራዊ እንዲሆን ድጋፍ እንደምታደርግ ገልፀዋል፡፡

ሚኒስትሩ ግጭት በተከሰተባቸው አካባቢዎች የዜጎች ደህንነት እንዲረጋገጥ እና የሰብአዊ መብቶች እንዲከበሩ ሁለቱም ወገኖች የበኩላቸውን ሚና እንዲወጡም ጥሪ አቅርበዋል።

የሰላም ስምምነቱ ተግባራዊ  እንዲሆን የአፍሪካ ህብረት ያደረገውን ጥረት ያደነቁት ሚኒስትሩ የመላው ኢትዮጵያውያንን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ከአፍሪካ ህብረት እና አጋር አካላት ጋር በጋራ ለመስራት ዝግጁ መሆናቸውን አስታውቀዋል።

በአፍሪካ ግጭቶችን ለመከላከል፣ የአስተዳደር ችግሮችን ለመፍታት እና እና በአህጉሪቱ ሰላም እና ደህንነት ለማረጋገጥ አሜሪካ የአፍሪካ ህብረትን ተልዕኮ መደገፏን ትቀጥላለች ማለታቸውን ከአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.