Fana: At a Speed of Life!

በሰሜኑ የሀገሪቱ ክፍል በጦርነቱ ለተጎዱ ዜጎች ሁለተኛው ዙር የሰብዓዊ ድጋፍ እየቀረበ ነው – ኮሚሽኑ

አዲስ አበባ፣ ታኅሣሥ 21፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በሰሜኑ የሀገሪቱ ክፍል በጦርነቱ ጉዳት ለደረሰባቸው ዜጎች ሁለተኛው ዙር ሰብዓዊ ድጋፍ እየቀረበ መሆኑን የኢትዮጵያ አደጋ ሥጋት አመራር ኮሚሽን ገለጸ።

የኢትዮጵያ አደጋ ሥጋት አመራር ኮሚሽን አምባሳደር ሺፈራው ተክለማርያም በሰጡት መግለጫ እንዳሉት÷ በአማራ፣ በአፋርና በትግራይ ክልሎች በመጀመሪያው ዙር የታቀደውን ሰብዓዊ ድጋፍ ሙሉ በሙሉ ተደራሽ ማድረግ ተችሏል ።

በመጀመሪያው ዙር ድጋፍ 141 ሺህ 671 ሜትሪክ ቶን ምግብ ወደ ሦስቱም ክልሎች መጓጓዙን ነው የገለጹት፡፡

በሁለተኛው ዙር ደግሞ እስካሁን ወደ አማራ ክልል 25 ሺህ ሜትሪክ ቶን፣ ወደ አፋር ክልል 2 ሺህ ሜትሪክ ቶንና ወደ ትግራይ ክልል ደግሞ ከ1 ሺህ ሜትሪክ ቶን በላይ እህል ተጓጉዟል ብለዋል።

ይህም በሁለተኛው ዙር ድጋፍ ለማድረግ ከታቀደው 20 በመቶ መሆኑን ጠቁመው÷ ቀሪውን ድጋፍ ለማድረግ የሚሰሩ ሥራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ አብራርተዋል።

ድጋፎቹ በአራት ኮሪደሮች እየቀረበ መሆኑን እና መልሶ ማቋቋሙን በተመለከተም የሚኒስትሮች ኮሚቴ ተቋቁሞ እየተሰራ መሆኑንም አስገንዝበዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.