Fana: At a Speed of Life!

ኢንስቲትዩቱ  እና የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ በጋራ ለመስራት የሚያስችላቸውን የስምምነት ሰነድ ተፈራረሙ

አዲስ አበባ፣ ታኅሣሥ 21፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት እና የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ በጋራ ለመስራት የሚያስችላቸውን የስምምነት ሰነድ ተፈራርመዋል።

የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር ኢንጅነር ወርቁ ጋቸና  በፊርማ ስነ ስርዓቱ ወቅት እንደገለፁት÷ ስምምነቱ  ሁለቱ ተቋማት ያላቸውን አቅም አቀናጅቶ ለመስራት ያግዛል፡፡

ለዚህም በቴክኖሎጂ አቅርቦትና ተጠቃሚነት እንዲሁም በሰው ኃይል ልማት በኩል ኢንስቲትዩቱ ከኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ጋር  ተቀናጅቶ ለመስራት ቁርጠኛ መሆኑን አስረድተዋል።

የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገብረ ሚካኤል በበኩላቸው÷ስምምነቱ ሁለቱ ተቋማት ለሀገር የሚያበረክቱትን አስተዋፅኦ በቴክኖሎጂ የታገዘ ለማድረግ እንደሚያስችል አመላክተዋል።

በተጨማሪም ስትራቴጂክ  በሆኑ ጉዳዮች ተቀራርቦ በመስራት ለምስራቅ አፍሪካ ቀጠናም የደህንነት ስጋትን ለመቀነስ የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ቴክኖሎጂ ሚና ወሳኝ መሆኑን ኮሚሽነር ጀነራሉ  መናገራቸውን ከኢንስቲትዩቱ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.