Fana: At a Speed of Life!

ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን ከኦሮሚያ ክልል አመራሮች እና የሕዝብ ተወካዮች ጋር እየተወያየ ነው

አዲስ አበባ ፣ ታኅሣሥ 22 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን ከኦሮሚያ ክልል አመራሮች እና የሕዝብ ተወካዮች ጋር በአዳማ እየተወያየ ነው።

ውይይቱ በቀጣይ ሊደረግ ለታቀደው ምክክር የተሳታፊዎች ልየታ እና አጀንዳ አሰባሰብን የተመለከተ መሆኑን የኦ ቢ ኤን ዘገባ ያመላክታል።

ሀገራዊ ምክክሩን አካታች እና አሳታፊ እንዲሁም ሕዝቡ በባለቤትነት እንዲመራው በማድረግ ውጤታማ እንዲሆን እየተሠራ መሆኑ በዚህ ወቅት ተገልጿል።

ኮሚሽነር ዘገየ አስፋው ምክክሩ የጋራ ተጠቃሚነት የሚረጋገጥበት መሆኑን ጠቅሰው፥ ሀገራዊ ኮሚሽኑ ገለልተኝነቱን ጠብቆ እንደሚሰራ ተናግረዋል።

ለሁለት ቀናት በሚቆየው ውይይት የምክክር ፅንሰ ሐሳብ፣ የምክክር ተሳታፊዎች ልየታ እና የውይይት አጀንዳዎች አሰባሰብን በተመለከተ በሚነሡ ጥያቄዎች ላይ ማብራሪያ ይሰጥባቸዋል ተብሏል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.