Fana: At a Speed of Life!

የመዲናዋ የተማሪ ወላጆች በብዝሃ ቋንቋ አተገባበር ጥናት ላይ ተወያዩ

አዲስ አበባ ፣ ታኅሣሥ 22 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ ከተማ በሁሉም ክፍለ ከተሞች የሚገኙ የተማሪ ወላጆች ከአፍ መፍቻ ተጨማሪ የሀገር ውስጥና የውጪ ቋንቋዎችን በትምህርት ስርዓቱ ለማካተት በተጠናው የብዝሃ ቋንቋ አተገባበር ጥናት ላይ ተወያይተዋል።

የብልጽግና ፓርቲ አዲስ አበባ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ መለሰ ዓለሙ በቪዲዮ ኮንፈረንስ ባስተላለፉት መልዕክት÷ ኢትዮጵያ ብዝሃነቷን አክብራና ተንከባክባ ከትውልድ ትውልድ እንድትሸጋገር የተለያዩ ስራዎች እየተሰሩ ነው ብለዋል፡፡

ኮተቤ ዩኒቨርስቲ ለብዝሃ ቋንቋ አተገባበር ያደረገው ጥናትን አስመልክቶ ወላጆች የሚሰጧቸው ሀሳቦች ለብዝሃ ቋንቋ አተገባበሩ እና ለመማር ማስተማሩ ሂደት ስኬታማነት እንደ ተጨማሪ ግብዓት እንደሚወሰዱ አቶ መለሰ ተናግረዋል።

ውይይትቱ ከቅርበት፣ ከተደራሽነት፣ ከተጠቃሚነት እንዲሁም ከማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና አስተዳደራዊ ጉዳዮች አንፃር የጥናቱ ውጤት ምን እንደሚመስል ከወላጆች ጋር የጋራ ለማድረግ እና ተጨማሪ ግብዓት ለማግኘት ታሳቢ ያደረገ ነው መባሉን የከንቲባ ጽ/ ቤት መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.