Fana: At a Speed of Life!

አቶ ሙስጠፌ መሀመድ በዶሎ ዞን የተለያዩ ፕሮጀክቶችን መረቁ

አዲስ አበባ ፣ ታኅሣሥ 22 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሙስጠፌ መሀመድ የሚመራ ልዑክ በዶሎ ዞን ወርዴር ከተማ የተለያዩ ፕሮጀክቶችን መርቆ ከፈተ።
 
ርዕሰ መስተዳድሩ በ100 ሚሊየን ብር ወጪ የተገነባው የወርዴር ሆስፒታልን እና የደም ባንክን መርቀው ስራ አስጀምረዋል፡፡
 
አቶ ሙስጠፌ በምረቃ ሥነ-ሥርዓት ላይ ባደረጉት ንግግር÷ባለፉት 30 ዓመታት በክልሉ 8 ሆስፒታሎች ብቻ እንደነበሩ ጠቁመው ከለውጡ ማግስት ብቻ 9 ደረጃቸውን የጠበቁ ሆስፒታሎች መገንባታቸውን አንስተዋል፡፡
 
የክልሉ ጤና ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ሙሳ አሕመድ በበኩላቸው÷ ሆስፒታሉ ለዶሎ ዞን እና አከባቢው የተሟላ አገልግሎት ይሰጣል ብለዋል።
 
በሌላ በኩል ርዕሰ መስተዳድሩ በ130 ሚሊየን ብር ወጪ የተደረገበት የወርዴር ከተማ የ24 ሰዓት የኤሌክትሪክ አገልግሎትንም መመረቃቸውን ከክልሉ ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
ባለፉት 4 የለውጥ ዓመታት ብቻ ከ66 የክልሉ ትላልቅ እና አነስተኛ ከተሞች የ24 ሰዓት የኤሌክትሪክ ተጠቃሚ ማድረግ መቻሉን አቶ ሙስጠፌ ገልጸዋል።
 
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
 
 
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.