Fana: At a Speed of Life!

አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ከዴንማርክ የልማት ትብብር ሚኒስትር ራስመስ ፕረህን ጋር በስልክ ተወያዩ

አዲስ አበባ፣መጋቢት 24፣2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኢፌዲሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ከዴንማርክ የልማት ትብብር ሚኒስትር ራስመስ ፕረህን ጋር በስልክ ተወያዩ።

በነበራቸው ቆይታም ሁለቱ ሀገሮች በትብብር መስራት በሚቻሉባቸው የተለያዩ ጉዳዮች ዙሪያ መምከራቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጽህፈት ቤት መረጃ ያመለክታል።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ገዱ ውይይቱ፥ በዴንማርክ በኮቪድ 19 የሞቱትን ሰዎች በተመለከተ ሃዛናቸውን ገልጸዋል።

ኮቪድ 19 ዓለም አቀፍ ችግር በመሆኑ የወረርሽኙን ስርጭት ለመግታት እና ብሎም ለመቆጣጠር የሁሉም አካላት ትብብርና ርብርብ ወሳኝ መሆኑንም አስታውቅዋል።

በተጨማሪም በኢትዮጵያ የኮቪድ 19 ስርጭትን ለመግታት በፌደራል እና በክልሎች እየተከናወኑ ያሉ የመከላከል እርምጃዎችን በቅንጅት እየተሰሩ ያሉ ሰራዎችን ገለፃ አድርገውላቸዋል።

የኮቪድ 19 ስርጭትን በምስራቅ አፍሪካ ቀጠና ለመግታት በኢጋድ ደረጃ በትብብር ለማከናወን የተደረሱ ስምምነቶችን በተመለከተም አቶ ገዱ ገለጻ አድርገዋል።

ዴንማርክ በምስራቅ አፍሪካ የተከሰተውን የበረሃ አንበጣ ለመከላከል በዓለም አቀፍ የምግብ እና የእርሻ ድርጅት /ፋኦ/ አማካኝነት እያደረገች ያለውን ድጋፍ በተመለከተም የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ገዱ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

ከዴንማርክ የልማት ትብብር ሚኒስትር ራስመስ ፕረህን በበኩላቸው፥ በኢትዮጵያ ስላለው ወቅታዊ ሁኔታ ስለተደረገላቸው ገለጻ አመስግነዋል።

ዴንማርክ የኮቪድ 19 ወረርሽኝን ለመግታት እያደረገች ያለውን እንቅስቃሴ በተመለከተ ማብራሪያ የሰጡት ሚኒስትሩ፥ የዓለም ስጋት የሆነውን የኮቨድ 19 ወረርሽኝ ለመግታት ዴንማርክ ከኢትዮጵያ ጋር በትብብር እንደምትሰራም ገልጸዋል።

የሁለቱ ሀገራት በሁለትዮሽ እና በዓለም አቀፍ መድረኮች የሚያደርጓቸውን ትብብሮች አጠናክረው እንደሚቀጥሉ እምነታቸው መሆኑን ገልጸዋል።

ዴንማርክ በምስራቅ አፍሪካ የበረሃ አንበጣን ለመከላከል እያደረገች ያለውን ድጋፍ አጠናክራ እንደምትቀጥልም አረጋግጠዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.