Fana: At a Speed of Life!

625 ኢትዮጵያውያን ከሳዑዲ ዓረቢያ ወደ ሀገራቸው ተመለሱ

አዲስ አበባ ፣ ታኅሣሥ 22 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በሳዑዲ ዓረቢያ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የነበሩ 625 ኢትዮጵያውያን በዛሬው ዕለት ወደ ሀገራቸው ተመልሰዋል፡፡

ከተመላሾቹ ውስጥ 613 ወንዶች፣ 9 ሴቶች፣ 3 ህፃናትና እድሜያቸው ከ18 ዓመት በታች የሆኑ ታዳጊዎች እንደሚገኙ ተገልጿል፡፡

ለተመላሽ ዜጎች በማቆያ ማዕከላት ተገቢውን ድጋፍ እና እንክብካቤ በማድረግ ከቤተሰብ ጋር የመቀላቀል ስራ እየተሰራ መሆኑንም የሴቶች እና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል፡፡

ከሕዳር 12 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ እስካሁን በተከናወነ ዜጎችን ወደ ሀገር የመመለስ ስራ 22 ሺህ 46 ኢትዮጵያውያንን መመለስ መቻሉ ተጠቁሟል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.