Fana: At a Speed of Life!

ወታደራዊ ኃይሉ በሱዳን ካለው የፖለቲካ ሂደት ለመውጣት ቁርጠኛ መሆኑን አልቡርሃን አረጋገጡ

አዲስ አበባ፣ ታኅሣሥ 23፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የሱዳን የሽግግር ሉዓላዊ ምክር ቤት ሊቀ መንበር አብዱልፈታህ አልቡርሃን ወታደራዊ ኃይሉ በሱዳን ካለው የፖለቲካ ሂደት ለመውጣት ቁርጠኛ መሆኑን አረጋገጡ፡፡

አል ቡርሃን ይህንን የገለፁት የሱዳን 67ኛ ዓመት የነጻነት በዓል ምክንያት በማድረግ ባደረጉት ንግግር ነው።

የሽግግር መንግሥቱ÷ ለኢኮኖሚያዊ ችግሮች አፋጣኝ መፍትሔዎችን ለማፈላለግ መርሐ ግብሮችን ለማዘጋጀት፣ የተሟላ የሰላም ግንባታ፣ ፀጥታና መረጋጋትን ለማስፈን እንዲሁም ሱዳንን ለምርጫ ዝግጁ ለማድረግ ያለመ እንደሚሆን ተስፋቻውን ገልጸዋል፡፡

የሀገር እና የፖለቲካ መሪዎች ሰልፎችን በማቀናጀት ለሀገር አንድነትና ግንባታ መሰረት እንዲጥሉ አልቡርሃን ጥሪ ማቅረባቸውን ሽንዋ ዘግቧል፡፡

በፈረንጆቹ ታኅሣሥ 5 ቀን 2022 የሱዳን ወታደራዊ እና ሲቪል መሪዎች የፖለቲካ አለመግባባቶችን ለማስወገድ እና የሁለት ዓመት የሽግግር ሲቪል ባለስልጣን ለማቋቋም የፖለቲካ ማዕቀፍ ስምምነት መፈራረማቸው ይታወሳል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.