Fana: At a Speed of Life!

አየር መንገዱ ወደ ሽረ እንዳስላሴ ዳግም በረራ ጀመረ

አዲስ አበባ፣ ታኅሣሥ 24፣ 2015 (ኤፍ ቢ) የኢትዮጵያ አየር መንገድ የሰላም ስምምነቱን ተከትሎ ወደ ሽረ እንዳስላሴ የሚያደርገውን በረራ በዛሬው ዕለት ጀምሯል፡፡

ባለፈው ሳምንት አርብ አየር መንገዱ ከአዲስ አበባ መቀሌ ዳግም መደበኛ በረራ መጀመሩ የሚታወስ ነው፡፡

ዛሬ በመጀመሪያው በረራ የተሳፈሩት እና የተለያዩ ቤተሰቦቻቸውን ለማግኘት ወደ ሽረ እንዳስላሴ መንገድ የጀመሩት ተጓዦች የአየር ትራንስፖርት በመጀመሩ መደሰታቸውን ተናግረዋል።

ይህ እውን እንዲሆን ያደረገው የፕሪቶሪያው የሰላም ስምምነት በመሆኑ ለስምምነቱ ተፈፃሚነት ሁሉም የበኩሉን ሚና መወጣት አለበት ብለዋል።

ጦርነት አውዳሚ መሆኑን ሁላችንም አይተነዋል ያሉት መንገደኞቹ ሰላም ካለ ሁሉን ማድረግ እንችላለንና ለሰላም ሁላችንም እንስራ ሲሉም መልዕክት አስተላልፈዋል።

በፀጋዬ ወንድወሰን

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.