Fana: At a Speed of Life!

በአዲሱ የፈረንጆቹ አመት ሲሶው የዓለም ኢኮኖሚ “በድቀት” ውስጥ ይቆያል – ዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት

አዲስ አበባ፣ ታኅሣሥ 24፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በተያዘው የፈረንጆቹ አዲስ ዓመት 1/3 የዓለም ኢኮኖሚ “ድቀት” ይገጥመዋል ሲል ዓለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም (አይ ኤም ኤፍ) አስጠነቀቀ።

የተቋሙ ዋና ዳይሬክተር ክርስታሊና ጆርጂዬቫ 2023 ከተጠናቀቀው አመት የባሰ የኢኮኖሚ ማሽቆልቆል እንደሚያጋጥመው ገልጸዋል።

ዋና ዳይሬክተሯ በአዲሱ የፈረንጆቹ አመት 1/3 የዓለም ኢኮኖሚ ድቀት እንደሚገጥመው እንጠብቃለን ብለዋል።

በንግግራቸው በኢኮኖሚ ድቀት ውስጥ በማይገኙ ሀገራት የሚኖሩ በሚሊየኖች የሚቆጠሩ ዜጎች የኢኮኖሚው ጫና ገፈት ቀማሾች እንደሚሆኑም ጠቅሰዋል።

አሜሪካ፣ የአውሮፓ ህብረት አባል ሀገራት እና ቻይና ኢኮኖሚያቸው እያሽቆለቆለ መሄዱንም ነው የገለጹት።

በተለይም ለቻይና አዲሱ አመት ፈታኝ መሆኑን ያነሱት ዳይሬክተሯ የመጀመሪያዎቹ ወራትም ለቤጂንግ ከባድ ይሆናሉ ሲሉ አስጠንቅቀዋል።

የቻይና፣ የቀጠናው ብሎም የዓለም ኢኮኖሚያዊ እድገት ነጌቲቭ ሊሆን እንደሚችል መናገራቸውን ቢቢሲ አስነብቧል።

የሩሲያ ዩክሬን ጦርነት፣ የሸቀጦች ዋጋ መናር፣ ከፍተኛ የወለድ ምጣኔ እና በቻይና ያለው የኮቪድ ስርጭት ለዓለም ኢኮኖሚ ማሽቆልቆል ምክንያት መሆናቸውን ተጠቅሷል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.