Fana: At a Speed of Life!

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የስራ ኃላፊዎችና የሚሲዮን መሪዎች የቦሌ-ለሚ ኢንዱስትሪ ፓርክን ጎበኙ

አዲስ አበባ፣ ታኅሣሥ 24፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር እና የተጠሪ ተቋማት የስራ ኃላፊዎች ከሚሲዮን መሪዎች ጋር በመሆን የቦሌ-ለሚ ኢንዱስትሪ ፓርክን ጎብኝተዋል።

በጉብኝታቸውም በኢንዱስቱሪ ፓርኩ  ውስጥ የሚገኙ የጨርቃ ጨርቅ ማምረቻ እና የብቅል ፋብሪካዎችን ተዘዋውረው ተመልክተዋል፡፡

የስራ ኃላፊዎቹ እና የሚሲዮን መሪዎቹ÷ በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን በኩል ሀገሪቱ በኢንቨስትመንት  ያላትን አቅም እና በዘርፉ እየተተገበረ ያለውን የሕግ ማሻሻያ በሚመለከት ገለፃ ተደርጎላቸዋል።

በተጨማሪም ኢንቨስትመንትን ወደ ኢትዮጵያ ለመሳብ በሚደረግ እንቅስቃሴ ወቅት የሚያጋጥሙ ማነቆዎች ላይ እንዲሁም በቀጣይ በትብብር መስራት በሚቻልባቸው ሁኔታዎች ዙሪያ ምክክር ተካሂዷል፡፡

በመድረኩ የተገኙት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ብርቱካን አያኖ÷ ኢንቨስትመንትን መሳብ የሚሲዮኖች ዋነኛ ተልዕኮ መሆኑን አስረድተዋል፡፡

በተለይ ሀገሪቱ ካለችበት ወቅታዊ ሁኔታ አንፃር ዲፕሎማቱ ዘርፉን ለማሳደግ በተለየ መልኩ ሊሰራ እንደሚገባ መግለጻቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.