Fana: At a Speed of Life!

በአሸባሪው ሸኔ ላይ እየተወሰደ ያለው እርምጃ መጠናከሩን ዘመቻውን የሚመሩ ከፍተኛ የመከላከያ መኮንን ተናገሩ

አዲስ አበባ፣ ታኅሣሥ 25፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በደቡባዊ ኦሮሚያና አዋሳኝ አካባቢዎች የተሰማራው መከላከያ ሰራዊት በአሸባሪው ሸኔ ይዞታ ስር የነበሩ ሰባት ቀበሌዎችን ማስለቀቅ መቻሉን ዘመቻውን የሚመሩ የመከላከያ ከፍተኛ መኮንን ተናገሩ፡፡

ዘመቻውን የሚመሩት ከፍተኛ የመከላከያ መኮንን እንዳሉት÷ አሸባሪው የሸኔ ታጣቂ ኃይል በኦሮሚያ ክልል የሚያደርሰውን ሕዝባዊ ጥፋት በመግታት የተረጋጋ ቀጠና ለመፍጠር እየተሠራ ነው፡፡

አሸባሪውን የሸኔ ታጣቂ ኃይል የመደምሰስ ዘመቻ አካል በሆነውና በደቡባዊ ኦሮሚያና አዋሳኝ አካባቢዎች የተሰማራው መከላከያ ሠራዊት በሸኔ ይዞታ ስር የነበሩ በርካታ ቀበሌዎችን ማስለቀቅ መቻሉን የመከላከያ ሠራዊት መረጃ አመላክቷል፡፡

በደቡባዊ ኦሮሚያ በሚገኙት በምዕራብና ምሥራቅ ጉጂ እንዲሁም ቦረና ዞኖችን ማዕከል አድርጎ የሚንቀሳቀሰው መከላከያ ሠራዊት ስኬታማ ተልዕኮ ላይ እንደሚገኝ ነው ከፍተኛ መኮንኑ ያረጋገጡት፡፡

መከላከያ ሠራዊቱ ባደረጋቸው የተጠኑ ዘመቻዎች ለዓመታት በአሸባሪው ሸኔ ይዞታ ስር የነበሩ ሰባት ቀበሌዎች ነፃ ማድረግ መቻሉን ነው የተናገሩት፡፡

የምሥራቅ ጉጂ አመራር እደገለጹት÷ የሕዝብና የሀገር ጠላት የሆነውን የሸኔ ታጣቂ ኃይል በማጥፋት ማህበረሰቡ ከስጋት ነፃ እንዲሆን እንደ ሠራዊቱ ሕዝቡ የዚህ ዘመቻ ግንባር ቀደም መሪ መሆን ይገባዋል።

ለሕዝብ ጥቅም እቆማለሁ በሚል ማጭበርበሪያ ማህበረሰቡን ለዘርፈ ብዙ ችግር የዳረገውን የሸኔ ኃይል ከቀጠናው ለማጥፋት በሚደረገው ትግል የሚጠበቅባቸውን እንደሚያደርጉም ነዋሪዎች ተናግረዋል።

የተጀመረው ዘመቻ በቀጠናው ስር ያለውን የሸኔ ታጣቂ ኃይል መደምሰስና የተረጋጋ ቀጠና መፍጠር ላይ ያተኮረ መሆኑ ተጠቁሟል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.