Fana: At a Speed of Life!

ከ43 ሚሊየን ሊትር በላይ የፓልም የምግብ ዘይት ግዢ ተፈጸመ

አዲስ አበባ፣ ታኅሣሥ 25፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ከ43 ሚሊየን ሊትር በላይ የፓልም የምግብ ዘይት ግዢ መፈጸሙን የገንዘብ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

ህብረተሰቡ በተመጣጣኝ ዋጋ የምግብ ዘይት አንዲያገኝ ጅቡቲ ከሚገኘው ጎልደን አፍሪካ ኩባንያ የ43 ሚሊየን 37 ሺህ 412 ሊትር የፓልም የምግብ ዘይት ግዢ መፈጸሙን የገንዘብ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

የግዢ ውሉን የተፈራረሙት የኢትዮጵያ የንግድ ሥራዎች ኮርፖሬሽንና የኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ግብአቶች ልማት ድርጅት ሲሆኑ÷ ለግዢ የሚውለውን የ69 ሚሊየን 894 ሺህ 440 የአሜሪካ ዶላር ለኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ዋስትና የሰጠው የገንዘብ ሚኒስቴር መሆኑ ታውቋል፡፡

የምግብ ዘይቱ ግዢ በአንድ ዓመት የክፍያ ጊዜ ይፈጸማል፡፡

ይህን የሀገር ውስጥ የምግብ ዘይት ዋጋን ለማረጋጋት ታስቦ የተፈጸመውን ግዢ ያስተባባረው የገንዘብ ሚኒስቴር÷ የግዢ ውሉን ለተፈራራሙት ለኢትዮጵያ የንግድ ሥራዎች ኮርፖሬሽንና ለኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ግብዓቶች ልማት ድርጅቶች በላከው ደብዳቤ በአዲስ አበባና ከአዲስ አበባ ከተማ ውጪ እሽግ የፓልም ምግብ ዘይት የመሸጫ ዋጋ እንደሚከተለው መሆኑን አስታውቋል፡፡

በዚህም መሰረት የአዲስ አበባ የፓልም ምግብ ዘይት መሸጫ ዋጋ

  • ባለ 3 ሊትር በጄሪካን …… ብር 314
  • ባለ 5 ሊትር በጄሪካን …… ብር 510
  • ባለ 20 ሊትር በጄሪካን …… ብር 2003 መሆኑ ታውቋል፡፡

ከአዲስ አበባ ውጪ ያሉ ከተሞችን በተመለከተም ርቀትን ታሳቢ በማድረግ የትራንስፖርት አገልግሎት ክፍያ ታሪፍ በኩንታል 60 ሳንቲም በአንድ ኪሎሜትር መሆኑ ታሳቢ ተደርጎ÷ ሽያጭ እንዲከናወንና የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴርም በተለመደው መልኩ የክልልና የከተማ አስተዳደሮችን የስርጭት ኮታ በመመደብ ለኢትዮጵያ የንግድ ሥራዎች ኮርፖሬሽንና ለኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ግብአቶች ልማት ድርጅት እዲያሳውቅ አቅጣጫ ተቀምጧል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.