Fana: At a Speed of Life!

የፌደራል የመሬት ባንክና ልማት ኮርፖሬሽን ከኢትዮ-ኢንጂነሪንግ ጋር በጋራ ለመሥራት የሚያስችላቸውን ሥምምነት ተፈራረሙ

አዲስ አበባ፣ ታኅሣሥ 25፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የፌደራል የመሬት ባንክ ልማት ኮርፖሬሽን እና ኢትዮ-ኢንጂነሪንግ ግሩፕ የተለያዩ የልማት ፕሮጀክቶችን በጋራ ለማከናወን የሚያስችላቸውን ሥምምነት ተፈራረሙ።

ሥምምነቱን የፌደራል የመሬት ባንክ ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ዳይሬክተር ሌንሳ መኮንንና የኢትዮ- ኢንጂነሪንግ ግሩፕ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አምባሳደር ምስጋኑ አረጋ መፈራረማቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

ሥምምነቱ በሀገሪቱ የተለያዩ የልማት ፕሮጀክቶችን ለማካሄድና የኢንቨስትመንት ሥራዎችን ለማሳደግ የሚያስችሉ ተግባራትን በጋራ ለማከናወን እንደሚያስችል ተጠቁሟል።

የፌደራል የመሬት ባንክና ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ዳይሬክተር ሌንሳ መኮንን በዚህ ጊዜ እንደገለጹት የሀገሪቱን ሁለንናዊ ልማት ለማረጋገጥ ቅንጅታዊ አሰራር ወሳኝ ነው።

ለዚህም ኮርፖሬሽኑ ከኢትዮ-ኢንጂነሪንግ ግሩፕ ጋራ በሀገሪቱ የተለያዩ የልማት ፕሮጀክቶችን በመቅረጽ ወደ ተግባር ለመለወጥ እንዲያስችል ሥምምነት መድረሱን ጠቁመዋል።

ሥምምነቱ በሀገሪቱ ኢንቨስትመንት ለመሳብ የሚያስችሉ ሥራዎችን በጋራ ለመሥራትም ትልቅ አቅም እንደሚፈጥርም ነው ያስረዱት።

የኢትዮ-ኢንጂነሪንግ ግሩፕ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አምባሳደር ምስጋኑ አረጋ በበኩላቸው ሥምምነቱ በሁለቱ ተቋማት በቅንጅት የሚሰሩ ፕሮጀክቶችን ለማፈላለግ ያግዛል ብለዋል።

ሥምምነቱ የተለያዩ ፕሮጀክቶችን በጋራ በማልማት ለዜጎች የሥራ እድል በመፍጠር ለሀገሪቱ ኢኮኖሚያዊ ዕድገት አስተዋጽኦ እንደሚኖረው ታምኖበታል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.