Fana: At a Speed of Life!

በፓን አፍሪካ የእግር ኳስ ውድድር ኢትዮጵያን ወክለው የሚወዳደሩ ትምህርት ቤቶች ታወቁ

አዲስ አበባ፣ ታኅሣሥ 25፣ 2015 ( ኤፍ ቢ ሲ) ገዳ ሮበሌ አንደኛ ደረጃ እና አዋሮ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች በፓን አፍሪካ የእግር ኳስ ውድድር ኢትዮጵያን ወክለው እንደሚወዳደሩ ታውቋል፡፡

በኦሮሚያ ክልል አስተናጋጅነት ለሶስት ቀናት በአዳማ ከተማ ሲካሄድ የቆየው 2ኛው ከ16 አመት በታች የፓን አፍሪካ የትምህርት ቤቶች የእግር ኳስ የማጣሪያ ውድድር ዛሬ ተጠናቋል፡፡

በውድድሩም ኢትዮጵያን ወክለው በወንዶች ገዳ ሮበሌ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት እንዲሁም በሴቶች አዋሮ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ከኦሮሚያ ክልል አሸናፊ በመሆን መለየታቸውን ከትምህርት ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.