Fana: At a Speed of Life!

“ስለኢትዮጵያ” የፎቶግራፍ አውደ ርዕይና የፓናል ውይይት በሠመራ እየተካሔደ ነው

አዲስ አበባ ፣ ታኅሣሥ 26 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ያዘጋጀው 13ኛው “ስለኢትዮጵያ” የፎቶግራፍ አውደ ርዕይ እና የፓናል ውይይት በአፋር ክልል ሠመራ ከተማ እየተካሔደ ነው።

ከ1950ዎቹ ጊዜያት አንስቶ በየዘመኑ የነበሩ የኢትዮጵያ ፖለቲካ ወሳኝ ሁነቶች፣ በታሪክ አንጓዎች የተከሰቱ የሕዝብ ጥያቄዎች፣ ለሀገር ሉዓዊነት የተከፈሉ መስዋዕትነቶችና ከኢትዮጵያ የልማት ጉዞዎች ጋር ተያያዥነት ያላቸው አንኳር ሀገራዊ ክንውኖችን የሚያሳዩ ፎቶግራፎች ለዕይታ ቀርበዋል።

በዕለቱ በኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት አማካኝነት በአፋርኛ ቋንቋ ለመጀመሪያ ጊዜ የተዘጋጀው አሻራ መጽሃፍ በዕለቱ እንግዶች ተመርቋል።

“ሠላም አንድነት ልዕልና ስለኢትዮጵያ” በሚል ርዕስ የሚካሄደው የፓናል ውይይትም ተጀምሯል፡፡
 
የአፍሪካ ልዕቀት አካዳሚ ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ምህረት ደበበ÷ሰላም ከግለሰብ አንስቶ እስከ ሀገር ያለው ዋጋ ምን ይመስላል ፣ ለሰላም እንዴት ነው ጀግና መሆን የምንችለው የሚለው ላይ ትኩረት በማድረግ በተለይም ሰላም እና አንድነትን ስናሰፍን የልዕልናን ፍሬ እንበላለን ብለዋል።
 
የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ አወል አርባ÷ የሰላምን አስፈላጊነት ባሳለፍነው ጦርነት ባጣናቸው ነገሮች ማየት ችለናል፤ ሰላምና አንድነት ላይ በመስራት ሀገራችን መጠበቅና ማደግ ይገባናል ሲሉ ገልጸዋል።
 
የጠቅላይ ሚኒስትሩ የማህበራዊ ጉዳዮች አማካሪ ዲያቆን ዳንኤል ክብረት እና የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) አባል የሺዋስ አሰፋን ጨምሮ ሌሎች እንግዶች በምክክር መድረኩ ላይ ተሳትፈዋል።

 

በቅድስት ተስፋዬ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.