Fana: At a Speed of Life!

የትግራይ ክልልን ለማረጋጋትና መልሶ ለማቋቋም አስተዋፅኦ ላደረጉ አመራሮች እውቅና ተሰጠ

አዲስ አበባ ፣ ታኅሣሥ 26 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ አደም ፋራህ በተገኙበት የትግራይ ክልልን ለማረጋጋት እና መልሶ ለማቋቋም አስተዋፅኦ ላደረጉ አመራሮች የእውቅና መርሐ ግብር ተካሂዷል።
 
በርካታ አመራሮች በከፍተኛ ቁርጠኝነት የሕይወት መሥዋዕትነት በመክፈል ጭምር በሰሜኑ የሀገሪቱ ክፍል ተፈጥሮ የነበረው ችግር እልባት እንዲያገኝ ሲንቀሳቀሱ መቆየታቸው ተመላክቷል፡፡
 
የተደረሰው ጉዳት በአፋጣኝ እንዲያገግም፣ የሰብዓዊ ድጋፍ ያለገደብ እንዲደርስ፣ ሕዝቡ መሠረታዊ የሆኑ ፍላጎቶቹ እንዳይጓደልበት እንዲሁም የሰላም ስምምነቱ ከተፈረመ በኋላ ወደ ሥራ እንዲገባ በማድረግ በርካታ የብልጽግና ፓርቲ አመራሮች ጥረት ሲያደርጉ እንደነበርም ተጠቅሷል፡፡
 
ይህም አሁን ላይ በክልሉ ለተፈጠረው ሰላም ከፍተኛ አስተዋጽኦ ማበርከቱን ነው በመርሐ ግብሩ ላይ የተገለጸው፡፡
 
የተልዕኮ አፈፃፀም እና አጠቃላይ ቆይታ በሽረ እና አላማጣ በኩል ተልዕኮውን ወስደው በሄዱ አመራሮች በኩል አጭር ሪፖርት ቀርቧል፡፡
 
ኢትዮጵያን ማዳን የቻለ፣ የሕዝቦቿን አንድነት መጠበቅ የቻለ፣ ሕዝብን ከሰቆቃ መታደግ የቻለ ገድል በተሳታፊ አመራሮች በኩል እንደተፈጸመ መገለጹን ከፓርቲው ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
 
አቶ አደም ፋራህ÷ ተልዕኮውን ወስደው ለሄዱ አካላት ምስጋና ያቀረቡ ሲሆን÷ “የተሰጣችሁን ተልዕኮ ተቀብላችሁ ያስመዘገባችሁት ውጤት ሀገራችሁን እና ፓርቲያችሁን ለማገዝ ቆራጥነታችሁን እንዲሁም ዝግጁ መሆናችሁን አሳይታችኋል” ብለዋል።
 
 
 
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.