Fana: At a Speed of Life!

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ እና ኦሮሚያ ክልል ተጎራባች አካባቢዎች በግጭት ምላሽና ሠላም ግንባታ የሚሠራ ፕሮጀክት ይፋ ሆነ

አዲስ አበባ ፣ ታኅሣሥ 26 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በቤኒሻንጉል ጉሙዝ እና ኦሮሚያ ክልል ተጎራባች አካባቢዎች በግጭት ምላሽ አሠጣጥ እና ሠላም ግንባታ ላይ የሚሠራ ፕሮጀክት ይፋ ሆነ።

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል በባምባሲ፣ ቡልድግሉ እና ሸርቆሌ ወረዳዎች ለሚተገበረው ፕሮጀክት ከ5 ነጥብ 3 ሚሊየን ብር በላይ በጀት አንደተያዘም ነው የተገለጸው።

ባለፉት ዓመታት በተፈጠሩት የጸጥታ ችግሮች የደረሰውን ሞት፣ መፈናቀልና ዘርፈ-ብዙ ጉዳት መነሻ አድርጎ የተቀረጸው ፕሮጀክቱ ÷ የግጭት መነሻ የሆኑ ችግሮችን በመለየት ለዘላቂ ሠላም ግንባታ ይሠራል ተብሏል።

ፕሮጀክቱ በቀጥታ ተጠቃሚ ከሚያደርጋቸው 1 ሺህ 280 ዜጎች ባሻገር ቀጥተኛ ባልሆነ መልኩ ከ42 ሺህ 500 በላይ የህብረተሠብ ክፍሎችን ተጠቃሚ እንደሚያደርግም ነው የተጠቆመው።

አሁን የሚተገበረው ፕሮጀክት በሠላም ግንባታና ግጭት አፈታት ዙሪያ የሲቪክ ማኅበረሰብ ድርጅቶች በጋራ ተቀናጅተው እንዲሠሩ የሚያደርግ እንደሆነ ተገልጿል።

ፕሮጀክቱ የአምስት ወራት ቆይታ እንዳለው የተገለጸ ሲሆን ፥ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ እና በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ወለጋ ዞን ይተገበራልም ነው የተባለው፡፡

መሠል ፕሮጀክት በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ወለጋ ዞን መነሲቡ ወረዳ እንደሚተገበር መገለጹን ከቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ኮሙኒኬሽን ጽ/ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.