Fana: At a Speed of Life!

የቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ተርሚናል 1 የማሻሻያ ግንባታው ተጠናቆ ለአገልግሎት ክፍት ሆነ

አዲስ አበባ ፣ ታኅሣሥ 26 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ የሀገር ውስጥ በረራ የመንገደኞች ማስተናገጃ ተርሚናል ሲካሄድለት የነበረው የማሻሻያ ግንባታ ተጠናቆ ለአገልግሎት ክፍት ሆነ።

የመንገደኞች ማስተናገጃ ተርሚናል አንድ በግንባታ ላይ በነበረበት ወቅት የሀገር ውስጥ መንገዶች የዓለም አቀፍ በረራዎች ተጓዦች የሚጠቀሙበትን ተርሚናል ሁለት ሲጠቀሙ ቆይተዋል።

በቻይናው ኮሙኒኬሽን ኮንስትራክሽን ኩባንያ (ሲሲሲሲ) ግንባታው የተከናወነው ተርሚናል አንድ በ16 ሺህ 689 ካሬ ሜትር ስፋት ላይ ያረፈ መሆኑን ከግንባታው ተቋራጭ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.