Fana: At a Speed of Life!

በኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበር ፕሬዚዳንት የተመራ ልዑክ መቀሌ ገባ

አዲስ አበባ ፣ ታኅሣሥ 26 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበር ፕሬዚዳንት አቶ አበራ ቶላ የተመራ የማኅበሩ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ልዑክ መቀሌ ከተማ ገብቷል።
 
የልዑካን ቡድኑ አባላት መቀሌ አሉላ አባ ነጋ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ በማኅበሩ የትግራይ ክልል ቅርንጫፍ ጽ/ ቤት ቦርድ ሰብሳቢ የማነ ዘርዓይን ጨምሮ የቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ የሥራ ኃላፊዎች አቀባበል አድርገውላቸዋል።
 
ልዑኩ በቆይታው ለቅርንጫፍ ጽህፈት ቤቱ የተሽከርካሪዎች ርክክብ የሚያደርግ መሆኑን ከኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
 
በተጨማሪም ማኅበሩ በክልሉ እያከናወነ ባለው ሰብዓዊ አገልግሎትና ቀጣይ ሰብዓዊ ድጋፍ በሚደረግበት ሁኔታ ላይ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር እንደሚመክር ይጠበቃል፡፡
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.