የዓለም ባንክ ኢትዮጵያ የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመግታት ለምታደርገው ጥረት የሚውል የ82 ሚሊየን ዶላር ድጋፍ አደረገ
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 24፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የዓለም ባንክ ኢትዮጵያ የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመግታት ለምታደርገው ጥረት የሚውል የ82 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር ድጋፍ አደረገ።
ድጋፉ ኢትዮጵያ የቫይረሱን ስርጭት በመቆጣጠር በአጭር ጊዜ ውስጥ ማገገም እንድትችል በሚያግዙ ዘርፎች ላይ እንደሚውል አስታውቋል።
የገንዘብ ድጋፉ የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመከላከል ለሚያስችሉ መድሃቶች እና የጤና ቁሳቁሶች ማሟያ፣ አዲስ ለሚቋቋሙ የለይቶ ማቆያ እና ህክምና ማእከላት፣ ለስልክ ጥሪ ማእከላት እና መረጃን ለህብረተሰቡ ለማድረስ ለሚደረጉ ስራዎች ይውላል ነው የተባለው።
የባንኩ የዳይሬክተሮች ቦርድ ለአስቸኳይ ጊዜ ድጋፍ በሚል ባፀደቀው የፋይንስ ድጋፍ ከኢትዮጵያ በተጨማሪ ለህንድ የ1 ቢሊየን ዶላር፣ ለፓኪስታን 200 ሚሊየን ዶላር እና ለሌሎች ሀገራት ድጋፍ አድርጓል።