Fana: At a Speed of Life!

135 ሺህ 487 ሜትሪክ ቶን ምግብና ምግብ ነክ ያልሆነ እርዳታ እንዲሁም 879 ሺህ 980 ሊትር ነዳጅ ወደ ትግራይ ተልኳል

አዲስ አበባ፣ ታኅሣሥ 27፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) እስካሁን 135 ሺህ 487 ሜትሪክ ቶን ምግብና ምግብ ነክ ያልሆነ እርዳታ እንዲሁም 1 ነጥብ 1 ቢለየን በላይ ብር ወደ ትግራይ ክልል መላኩን የአደጋ ስጋት አመራር ኮሚሽን አስታውቋል፡፡
 
የሰላም ስምምነቱን ተከትሎ መንግስት ከአጋር አካላትጋር በመተባበር ወደ ትግራይ ክልል የሚያደርሰው የሰብዓዊ እርዳታ አቅርቦት ተጠናክሮ መቀጠሉ ተገልጿል፡፡
 
እስካሁን ድርስም 135 ሺህ 487 ሜትሪክ ቶን ምግብና ምግብ ነክ ያልሆነ ዕርዳታ ወደ ትግራይ ክልል መላኩን የኮሚሽኑ የሕዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር ደበበ ዘውዴ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ተናግረዋል፡፡
 
በተመሳሳይ ለስራ ማስኬጃ የሚውል 1 ነጥብ 1 ቢሊየን በላይ ብር ወደ ትግራይ ክልል መላኩ ነው ኮሚሽኑ ያስታወቀው፡፡
 
በሌላ በኩል 879 ሺህ 980 ሊትር ነዳጅ ወደ ትግራይ ክልል የተላከ ሲሆን ÷ 3ሺህ 389 ተሽከርካሪዎች ወደ ክልሉ መጓጓዛቸው ተጠቁሟል፡፡
 
እስከ ታህሳስ 25 ቀን 2015 ዓ.ም ድረስም 26 የሰብዓዊ እርዳታ በረራዎች መደረጋቸውን አቶ ደበበ አንስተዋል፡፡
 
በክልሉ የሰብዓዊ እርዳታ የሚያሰራጩ አጋር አካላት ቁጥርም 119 መድረሳቸው ነው የተመላከተው፡፡
 
በመላኩ ገድፍ
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.