Fana: At a Speed of Life!

በራህሌ ከተማና አካባቢዋ ዳግም የኤሌክትሪክ ኃይል አገኙ

አዲስ አበባ፣ ታኅሣሥ 27፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ከሁለት ዓመታት በላይ የኤሌክትሪክ አገልግሎት ተቋርጦባቸው የነበሩት በራህሌ ከተማና አካባቢዋ ዳግም የኤሌክትሪክ ኃይል አገኙ፡፡

በግጭቱ ምክንያት በኤሌክትሪክ መሰረተ ልማት ላይ በደረሰው ጉዳት ከሁለት ዓመታት በላይ ተቋርጦ የነበረው የበራህሌ ወረዳ ዳግም የኤሌክትሪክ ኃይል ማግኘቱን ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

አገልግሎቱን ዳግም ማስጀመር የተቻለው÷ የመከከለኛና የዝቅተኛ የኤሌክትሪክ መስመሮችን እና ትራንስፎርመሮች እንደገና በመጠገን ነው፡፡

በኪልበቲ ረሱ የሚያገኙ ከተሞችም ዳግም የኤሌክትሪክ አገልግሎት እንዲያገኙ እየተሠራ መሆኑ ተገጿል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.