Fana: At a Speed of Life!

አቶ ደስታ ሌዳሞ ለመላው የክርስትና ዕምነት ተከታዮች የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ

አዲስ አበባ፣ ታኅሣሥ 27፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የሲዳማ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ርዕሰ መስተዳድር አቶ ደስታ ሌዳሞ ለመላው የክርስትና ዕምነት ተከታዮች የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ፡፡

ርዕሰ መስተዳድሩ በመልዕክታቸው ፥ ኢየሱስ የተወለደበት ሚስጥር የሰው ልጆች በምድር ላይ መኖር ከጀመሩበት ጊዜ አንስተው የተሰጣቸውን ትእዛዝ በመተላለፍ ኃጥኣት በመስራት ከታጩት ዘላለማዊ ህይወት ወደ ጥፋት መንገድ በመሄዳቸው፤ ይህንን ለማስታረቅ መሆኑን ርዕሰ መስተዳድሩ ገልጸዋል፡፡

ዕለቱ የሰው ልጆች ለሰሩት ኃጥኣት ኢየሱስ ማስተሰሪያ በመሆን የዘላለምን ህይወት እንዲወርሱ የተወለደበትን የምናከብርበት መሆኑንም የጠቆሙት ርዕሰ መስተዳድሩ ፥ በመወለዱም የሰው ልጆች እርግማን ተሰብሯል፤ የሰው ልጆች ዳግም ኃጥኣት እንዳይሰሩ ትእዛዝ ተላልፏል ብለዋል፡፡

ክርስቶስ መወለዱ በፍቅር እንድንኖር፤ መከባበርንና መቻቻል እንዲሰፍን ለዛሬው ትውልድ ትምህርት የሰጠ መሆኑን ተናግረው፤ ጥላቻን፣ መገፋፋትን፣ አንዱ ሌላውን መበደል በዚህ ትውልድም መኖር እንደሌለበት አሳስበዋል፡፡

በዓሉን በምናከብርበት ጊዜ እርስ በርስ በመተሳሰብ፣ በፍቅር፣ ያለው የሌለውን በመርዳት መሆን እንዳለበት ነው የጠየቁት፡፡

በበዓሉ ወቅት በክልሉ ምንም ዓይነት የጸጥታ ችግር እንዳይፈጠር እና ህብረተሰቡ በሰላም በዓሉን እንዲያከብር በቂ ቅድመ ዝግጅት መደረጉን ገልፀዋል፡፡

መላው የክልሉ ነዋሪዎች ጉዳዩ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመቀናጀት የአከባቢያቸውን ደህንነት መጠበቅ እንዳለባቸውም ነው የገለጹት፡፡

በዓሉ ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ የሰላም፣ የፍቅር፣ የአንድነት፣ የመቻቻልና የአብሮነት እንዲሆን መመኘታቸውን ከክልሉ ብልጽግና ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.