Fana: At a Speed of Life!

በጋራ የተመዘገቡ ድሎችን ለማፅናት የሚያስችል ምክክር ማካሄዳቸውን የአማራ እና የኦሮሚያ ብልፅግና ፅህፈት ቤቶች ሀላፊዎች ተናገሩ

አዲስ አበባ፣ ታኅሣሥ 27፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በጋራ የተመዘገቡ ድሎችን ለማፅናት እና ፈተናዎችን በወንድማማችነት ለመሻገር የሚያስችል ምክክር ማካሄዳቸውን የአማራ እና ኦሮሚያ ብልፅግና ፅህፈት ቤቶች ሀላፊዎች ተናገሩ።

ለዘላቂ ሠላም እና ሁለንተናዊ ብልፅግና በሚል መሪ ቃል በሁለቱ ክልሎች ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች የተመራው መድረክ ለሁለት ቀናት በባህርዳር የተካሄደ ሲሆን፥ የአማራ ክልል የዞን እና ወረዳዎች ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች እና የኦሮሚያ ክልል ብልፅግና ፓርቲ አመራሮች የተሳተፉበት ነው።

 

በመድረኩ ማጠቃለያ ላይ የክልሎቹ የብልፅግና ፓርቲ ፅህፈት ቤቶች ሀላፊዎች አቶ ግርማ የሺጥላ እና አቶ ፈቃዱ ተሠማ ለጋዜጠኞች መግለጫ ሠጥተዋል።

ሀገራዊ ለውጡን ከማምጣት ጀምሮ እስከ ብልፅግና ምስረታ ሀገራዊ ለውጡን ለማፅናት የሁለቱ ክልሎች ህዝቦች በህዝብ ለህዝብ እና የአመራር ለአመራር ግንኙነቶች የላቀ ሚና መጫወታቸውን አንስተዋል።

መድረኩ ባለፉት ጊዜያት በተከናወኑ ተግባራት የተገኙ ድሎች፣ያጋጠሙ ችግሮች እና መፍትሄዎች ላይ በመምከር አቅጣጫ ለማስቀመጥ ያለመ መሆኑን የአማራ ክልል ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት ሀላፊ አቶ ግርማ የሺጥላ ገልፀዋል።

የኦሮሚያ ክልል የብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ሀላፊ አቶ ፈቃዱ ተሠማ በበኩላቸው መድረኩ የአመራር አንድነትን የሚያጠናክር ብዥታዎችን የሚያጠራ እና የህዝብ ለህዝብ ግንኙነትን ማሳደግ የሚያስችል መግባባት የተደረሠበት ነው ብለዋል።

ሁለቱ ህዝቦች በጋራ ለሀገር ብልፅግና እና ለልማት ተሰልፈዋል፤ ለሀገር ክብር በአንድነት ተዋድቀዋል ያሉት አቶ ፈቃዱ፥ ይህን አንድነት ለማጠናከርና ለህዝብ የጋራ ተጠቃሚነት በጋራ ለመስራት ውሳኔዎችን አሳልፈናል ማለታቸውን ኢቢሲ ዘግቧል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.