Fana: At a Speed of Life!

መቀመጫቸውን አዲስ አበባ ያደረጉ የተለያዩ ሀገራት አምባሳደሮች ላሊበላ ገቡ

አዲስ አበባ፣ ታኅሣሥ 28፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) መቀመጫቸውን አዲስ አበባ ያደረጉ የተለያዩ ሀገራት አምባሳደሮች በገና በዓል ላይ ለመታደም ዛሬ ላሊበላ ከተማ ገቡ፡፡

የቱሪዝም ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ስለሺ ግርማ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደገለጹት፥ እስካሁን የአሥር ሀገራት አምባሳደሮች ላሊበላ ከተማ ገብተዋል፡፡

በኢትዮጵያ የአሜሪካ መንግስት ጉዳይ ፈፃሚ አምባሳደር ትሬሲ አን ጃኮብሰን ተወካይን ጨምሮ÷ የቤልጀየም፣ ኦስትሪያ፣ አውስትራሊያ፣ ሩዋንዳ፣ ሜክሲኮ፣ ቻይና፣ ታንዛኒያ፣ ደቡብ አፍሪካ እና ብራዚል አምባሳደሮች በቱሪዝም ሚኒስቴር አስተባባሪነት የልደት (ገና) በዓልን ለመታደም ላሊበላ መግባታቸውን ሚኒስትር ዴኤታው ተናግረዋል።

ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች እና አምባሳደሮቹ ላሊበላ አውሮፕላን  ማረፊያ ሲደርሱ፥ የላሊበላ ከተማ አስተዳደር፣ የሐይማኖት አባቶች እና የኪነጥበብ ባለሙያዎች አቀባበል አድርገውላቸዋል፡፡

አምባሳደሮቹ በላሊበላ ከተማ በሚኖራቸው ቆይታ፥ በገና በዓል ላይ ከመታደም በተጨማሪ በአካባቢው የሚገኙ የቱሪስት መስኅቦችን እንደሚጎበኙ ይጠበቃል፡፡

የአምባሳደሮቹ ወደ ላሊበላ ከተማ ማቅናት የቱሪዝም ዘርፉን ይበልጥ ለማነቃቃት እና ከሀገራቱ የሚመጡ ጎብኚዎችን ቁጥር ለማሳደግ እንደሚያግዝ ከቱሪዝም ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

በተጨማሪም የአካባቢውን ሰላማዊነት ለማሳየት እና በቱሪዝም ዘርፉ ላይ ሥራዎችን በጋራ ለመሥራት ከፍተኛ ሚና እንደሚኖረው ተመላክቷል፡፡

እንግዶቹ በላሊበላ በሚኖራቸው ቆይታ የኢትዮጵያን በጎ ገጽታ ለመገንባት፣ የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ እንዲሁም የሀገሪቱን የቱሪዝም መስኅቦች ለማስተዋወቅ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንደሚኖረውም ተጠቁሟል፡፡

በዮሐንስ ደርበው

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.