Fana: At a Speed of Life!

በዓሉን ስናከብር ልባችንን ለይቅርታ ክፍት አድርገን ሰላምና ወንድማማችነትን እየሰበክን መሆን አለበት – አቶ ሽመልስ አብዲሳ

አዲስ አበባ፣ ታኅሣሥ 28፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በዓሉን ስናከብር ልባችንን ለይቅርታ ክፍት አድርገን ሰላምን እና ወንድማማችነትን እየሰበክን መሆን አለበት ሲሉ የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳ ተናገሩ፡፡

ርዕሰ መስተዳድሩ የገና በዓል አስመልክተው የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

በመልዕክታቸው በሀገር ውስጥ እና በውጭ ሀገር ለሚገኙ የክርስትና እምነት ተከታዮች እንኳን ለገና በዓል በሰላም አደረሳችሁ ብለዋል፡፡

ርዕሰ መስተዳድሩ በሀገራችን የመከፋፈል ፣ የመገፋፋት ፣የመጠላለፍ፣ ይቅር ከማለት ጥላቻን ማስፋፋት፣ከመከባበር ይልቅ ማዋረድ እንዲሁም የህብረተሰቡን ዕሴትና ስነምግባር የሚሰብሩ ነገሮች ዛሬ ላይ ፈተና ውስጥ ከተውናል ነው ያሉት፡፡

ይህን በጥላቻ የተሞላ አካሄድ ለመቀየርና በሀገሪቱ ሰላም እና መረጋጋት እንዲሁም የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ እንዲያብብ የተጀመረውን ብልጽግና ጉዞ ከህብረተሰቡ ጋር እናስቀጥላለን ሲሉ አጽንኦት ሰጥተዋል፡፡

ተደምረን በይቅርታ መሻገር ሀገራችን የገጠማትን ፈተና ለመሻገር ቁልፍ ነው ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ÷ለዚህም የጥላቻን ድልድይ ሰብሮ የፍቅርን ድልድይ ለመገንባት በትጋት ይሰራል ብለዋል፡፡

በዓሉን ስናከብርም ልባችንን ለይቅርታ ክፍት አድርገን ሰላምን እና ወንድማማችነትን እየሰበክን መሆን አለበት ነው ያሉት አቶ ሽመልስ፡፡

በዓሉም የሰላም፣ የፍቅር፣ የአንድነት፣ መከባበርና የመተሳሰብ እንዲሆንም መልካም ምኞታቸውን ገልጸዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.