Fana: At a Speed of Life!

በትግራይ ክልል ትምህርት ለመጀመር በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ውይይት እና ምልከታ ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ ታኅሣሥ 28፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የትምህርት ሚኒስቴር ከፍተኛ የባለሙያዎች ቡድን በትግራይ ክልል ትምህርት ለመጀመር በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ውይይት እና ምልከታ አድርገዋል።

ቡድኑ ምልከታውን ያደረገው በማዕከላዊ ዞንና በሰሜን ምዕራብ ዞኖች ባሉ የመጀመሪያና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች እንዲሁም በአክሱም ዩኒቨርሲቲ ሽረ እና ዓድዋ ካምፓሶች ነው።

በዚህም በዞኖቹ ትምህርት ለማስጀመር ባሉ አስቻይ ሁኔታዎችና ትምህርት ቤቶቹ ባሉበት ሁኔታ ከየዞኖቹ የትምህርት ስራ አመራሮችና ባለሙያዎች ጋር መወያየቱን የትምህርት ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል፡፡

ከሁለተኛ እና አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ርዕሰ መምህራን ፣ ምክትል ርዕሰ መምህራን ፣ ሱፐርቫይዘሮች እንዲሁም ከዩኒቨርሲቲ አመራሮች ጋር በተደረገው ውይይት ትምህርት ለመጀመር እንደሚቻል ተጠቁሟል።

በውይይቶቹም በትምህርት ቤቶች እና ዩኒቨርሲቲዎች የተፈጸሙ ዘረፋዎችና ትምህርት ቤቶች የተፈናቃዮች ማረፊያዎች መሆናቸውና ሌሎችም ተግዳሮቶች ቢኖሩም ተቋርጦ የነበረውን ትምህርት እንዲጀመር ከፍተኛ ፍላጎት መኖሩ ተመለክቷል።

በመሆኑም የተጓደሉ መሰረታዊ ግብአቶች ተሟልተው በአጭር ጊዜ በዞኖቹ የተቋረጠው ትምህርት ሊጀመር እንደሚገባ በምልከታው ወቅት መግባባት ላይ ተደርሷል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.