Fana: At a Speed of Life!

ጠ/ሚ ዐቢይ ከአውሮፓ ህብረት ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 25 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከአውሮፓ ህብረት ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ቻርልስ ሚሼል ጋር ኮቪድ19ን በተመለከተ ተወያይተዋል።

በውይይታቸው ኮሮና ቫይረስ በአፍሪካ ላይ የሚያስከትለውን ጉዳት ለመከላከል ከአውሮፓ ህብረት ጋር መስራት በሚቻልባቸው አግባቦች ዙሪያ መምከራቸውን በፌስ ቡክ ገጻቸው አስፍረዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ የአውሮፓ ህብረት ምክር ቤት እና የአውሮፓ ኅብረት ኮሚሽን ለአፍሪካ ድጋፍ ለመስጠት ዝግጁ በመሆናቸው ምስጋና አቅርበዋል።

ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ!
https://t.me/fanatelevision

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.