Fana: At a Speed of Life!

አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ከኖርዌይ አቻቸው ጋር በስልክ ተወያዩ

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 25 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢፌዴሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው የኮቪድ 19 ስርጭትን በጋራ መግታት በሚቻልባቸው ጉዳዮች ዙሪያ ከኖርዌይ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ኢን ማሪ ኤሪክሰን ሶሪድ ጋር በስልክ ተወያይተዋል።

አቶ ገዱ ኢትዮጵያ የኮቪድ 19 ስርጭትን ለመግታት እያደረገች ያለውን እንቅስቃሴ በተመለከተ ለሚኒስትሯ ገለፃ አድርገውላቸዋል።

በተጨማሪም የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት /ኢጋድ/ አባል ሃገራት መሪዎች የኮቪድ 19 ስርጭትን በትብብር ለመግታት ያሳለፉትን ውሳኔ እና እያደረጉ ያለውን እንቅስቃሴ በተመለከተም ገልጸውላቸዋል።

የኖርዌይ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ኢን ማሪ ኤሪክሰን ሶሪድ በበኩላቸው፥ የኮቪድ 19 ስርጭትን ለመግታት ትብብር አስፈላጊ መሆኑን ጠቅሰዋል።

ኖርዌይ ስርጭቱን ለመግታት ከአውሮፓ ህብረት እና ከዓለም የጤና ድርጅት ጋር በቅርበት እየሰራች መሆኗንም ሚኒስትሯ ገልጸዋል።

የኖርዲክ አባል ሃገራት የኮቪድ ስርጭትን ለመግታታ እያከናወኑ ያለውን የጋራ እንቅስቃሴ በተመለከተ ገለጻ ማድረጋቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ፅህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመግታት እና ለመቆጣጠርም ኖርዌይ ከኢትዮጵያ ጋር በትብብር እንደምትሰራ ሚኒስትሯ በነበራቸው የስልክ ውይይት አረጋግጠዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.