Fana: At a Speed of Life!

በሶማሌ ክልል የልማትና የመልካም አስተዳደር እቅድና ትግበራ ላይ ውይይት ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ ታኅሣሥ 29፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ)የሶማሌ ክልል የቀጣይ ሶስት አመታት የልማትና የመልካም አስተዳደር እቅድና ትግበራ ላይ ያተኮረ ውይይት በኤረር ዞን በፊቅ ከተማ ተካሂዷል።

ውይይቱን የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሙስጠፌ መሀመድ የመሩ ሲሆን÷ የክልሉ ምክትል ርእሰ መስተዳድር አቶ ኢብራሂም ኡስማንና የክልሉ ምክር ቤት አፈጉባኤ አያን አብዲን ጨምሮ ሌሎች የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች ተገኝተዋል።

በውይይቱ ለህዝብ የሚሰጡ መንግስታዊ አገልግሎቶችና የመልካም አስተዳደር ስራዎች የተገመገሙሲሆን÷ ተገልጋዩ ማህበረሰብ የሚያስደስት ግልጋሎት ያገኝ ዘንድ ከአመራሩ ብዙ እንደሚጠበቅ አቅጣጫ ተሰጥቷል።

በሌላ በኩል የክልሉ ሰላምና ፀጥታ እንዲሁም የፍትህ ሁኔታ ያለበት ደረጃ የተገመገመ ሲሆን÷ አሁን ያለውን አስተማማኝ ሰላም የበለጠ እንዲጠናከር አመራሩ ከህዝቡ ጋር የተቀናጀ ሥራ መሰራት እንዳለበት ተመላክቷል፡፡

የፍትህ ተቋማትም ለህዝቡ ገለልተኛ እና ፈጣን የፍትሕ አገልግሎት በመስጠት ረገድ በቀጣይ አመርቂ ውጤት እንደሚጠበቅ አቅጣጫ መቀመጡን ከክልሉ ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.