Fana: At a Speed of Life!

ጎንደር በጥምቀት በዓል ሰሞን በ100 ሺዎች የሚቆጠሩ እንግዶችን ለመቀበል የሚያስችላትን ዝግጅት ማድረጓ ተጠቆመ

አዲስ አበባ፣ ጥር 1፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በጥምቀት በዓል ሰሞን እስከ 2 ቢሊየን ብር በቱሪዝሙ ምክንያት ኢኮኖሚው ገቢ ያገኛል ተብሎ እንደሚጠበቅ የጎንደር ከተማ ባህልና ቱሪዝም መምሪያ ገለጸ፡፡

የመምሪያው ኃላፊ ቻላቸው ዳኜው ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንዳሉት÷ በጥምቀት በዓል ወቅት ከ750 ሺህ እስከ 1 ሚሊየን ጎብኚ ወደ ጎንደር እንደሚመጣ ይጠበቃል።

ለዚህም ከ400 በላይ ሆቴሎች እና ድንኳን የሚጣልባቸው ሥፍራዎች ዝግጁ መሆናቸውን አረጋግጠዋል፡፡

እንደ እንግዶች አቅም የማረፊያ፣ የምግብና መጠጥ መሸመቻ አማራጭ መሰናዳቱንም አስገንዝበዋል።

በሰሞነ ጥምቀት እስከ 2 ቢሊየን ብር በቱሪዝሙ ምክንያት ኢኮኖሚው ገቢ እንደሚያገኝ ጠቁመዋል።

ከ400 ዓመታት በላይ ያስቆጠረ ጥምቀተ ባሕርና የታቦታት ማደሪያ ሥፍራ መኖር ጥምቀትን በጎንደር ልዩ እንደሚያደርገው ገልጸዋል።

ይህም በተባበሩት መንግሥታት የትምህርት፣ ሣይንስ እና ባህል ድርጅት (ዩኔስኮ) በፈረንጆቹ1978 መመዝገቡን አስታውሰዋል።

ከጥር 4 እስከ 9 ቀን 2015 ዓ.ም በሚካሔደው የባህል ሣምንት፥ የአካባቢውን ብሎም የክልሉን ባህል፣ ወግና ትውፊት የሚያሳዩ ዝግጅቶች የሚቀርቡበት የአዝማሪ ፌስቲቫል አለ ብለዋል፡፡

ጥር 6 ቀን 2015 ዓ.ም የአጼ ቴዎድሮስ ልደት ሀገራዊ አንድነትን በሚያፀና ሁኔታ እንደሚከበር አመላክተዋል።

በዮሐንስ ደርበው

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.